የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት - በኢ/ኦ/ተ/ቤ የመንበረ ፓትርያርክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ አንድነቱ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ተቋማዊ ራእይ፣ ተልእኮ
      • መዋቅራዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቋማዊ አደረጃጀት
      • የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ
    • ስልታዊ እቅድ 2018 – 2021 ዓ/ም
  • ሥርዓተ ትምህርት
    • መሠረታዊ መረጃዎች
    • የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አደረጃጀት መመሪያ
    • የሥርዓተ ትምህርቱ መመማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
      • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
    • የሥርዓተ ትምህርቱ ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ /ካሌንደር
    • የመምህራን ሥልጠና እና መልእክቶች
    • መጻሕፍቱን ለማግኘት እና ተጨማሪ መረጃ
    • ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች
  • ፕሮጀክቶች
  • መዝሙረ ማኅሌት
    • የመስከረም ወር መዝሙሮች
      • የዮሐንስ መዝሙር
      • የመስቀል መዝሙሮች
      • የብዙኃን ማርያም መዝሙር (መስከረም ፳፩ )
      • የዘመነ ጽጌ መዝሙር
    • የጥቅምት ወር መዝሙሮች
      • የአብርሃ ወአጽብሐ መዝሙር (ጥቅምት 4 ቀን)
    • የኅዳር ወር መዝሙሮች
      • የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር (ኅዳር 12 ቀን)
    • የጥር ወር መዝሙሮች
      • የዘመነ ጥምቀት መዝሙር
      • የቃና ዘገሊላ መዝሙር (ጥር 12 ቀን)
    • የመጋቢት ወር መዝሙሮች
      • የወርኃ ጾም መዝሙሮች
      • የሆሣዕና መዝሙራት
      • የሰሙነ ሕማማት መዝሙሮች
  • ዜና
    • አጫጭር ዜናዎች
    • ዝርዝር ዜናዎች
    • ወቅታዊ መረጃዎች
    • ማስታወቂያ
      • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት እንግሊዝኛ ትርጉም ሥራ ተሳትፎ ጥሪ
  • ያግኙን
  • ቋንቋ
    • ትግርኛ
    • Afaanoromo
  • Menu Menu

የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣

ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣

የሰላም አለቃ፣የምሕረት አባት የሆነው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት የሆነችውን በዓለ ትንሣኤውን አክብረን ይህንን የረክበ ካህናት ቀኖናዊና ሲኖዶሳዊ ጉባኤ እንድናካሂድ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ለእሱ በማቅረብ፣እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

“ወይእዜኒ ንትልዋ ለሰላም በዘይት ሐነጽ ቢጽነ፡-እንግዲያው ስለሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምታነጽበትን እንከተል” (ሮሜ ፲፬፥፲፱)

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

በቅዱሳት መጻሕፍት በግልፅ እንደተቀመጠው እኛ የምናገለግላት ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል ናት፤ የተመሠረተችውም በደመ ክርስቶስ ነው፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ልትሰራው፣ልትጠብቀውና ልትፈጽመው የተሰጣት ዓቢይ ተልእኮ አለ፤ እሱም በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል ፍጹም ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ነው፡፡

ይህ ዓቢይ ተልእኮ የሰማይና የምድር መዝሙር ሆኖ ሁሌም በመደበኛ ይዘመራል፤ጌታችንም ከሞት ከተነሣ በኋላ ያሰማው የመጀመሪያ ድምጽ  “ሰላም ለእናንተ ይሁን”  የሚል ነው፡፡

የጌታ ምርጥ ንዋይ የተባለው ቅዱስ ጳውሎስም ”ሰላም የሚቆምበትን እንከተል” ሲል የሰላምን ተቀዳሚ አስፈላጊነት በአጽንዖት አስተምሮናል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሰላምን በቀዋሚ ምሰሶ አምሳላዊ ንጽጽር ገልፆአታል፡፡

ይህም ማለት ምሰሶ የቤትን ጣራ በቀዋሚነት ተሸክሞና ቀጥ አድርጎ እንደሚይዝ፣ሰላምም በተመሳሳይ የሰዎችን መንፈሳዊና አካላዊ ሕይወት ቀጥ አድርጋ የምትይዝና የምትጠብቅ መሆኗን ለመግለፅ እንደሆነ እንገነዘባለን።

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

እኛ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከኛ በታች ያሉ ውሉደ ክህነት፣እንዲሁም በእግዚአብሔር የልጅነት ጸጋ የከበሩ ምእመናንና ምእመናት ሁሉ፣ የቤተ ክርስቲያን መደበኛና ቀዋሚ ተልእኮ የሆነውን ሰላም የመጠበቅ፣ የማስጠበቅ፣ የማሥረጽና  የማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለብን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡

በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር፣ የመምከርና የማስታረቅ ኃላፊነት የእኛ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ዛሬ የተሰበሰብነው የተሰጠን አምላካዊ ተልእኮ ምን ያህል በተግባር አከናውነናል? ምን ሰርተናል? ምንስ ይቀረናል? ተልእኮአችንን ለመፈጸም በምናደርገው ጉዞስ ምን ችግር አጋጠመን? ችግሩን ለመፍታትስ ምን እናድርግ? የሚሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች በማንሣት በዝርዝርና በጥልቀት በማየት ተልእኮአችንን በኣግባቡ ለመወጣት ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናም ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የረክበ ካህናት ዓቢይ ጉባኤ እንዲደረግ ያዘዘበት ዋና ምክንያት ይህንን እንድናደርግ ነው፡፡

ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናችን እንደ ቤተ ክርስቲያን፣ሕዝባችንም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡

በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል፤የቤተ ክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተ ክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!

ጌታችን፡- “እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ” ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል፡፡በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም፡፡

በተለይም በትግራይና በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል፡፡በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል፡፡

እኛ ያጐደልነው፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል፡፡ ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሓ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም፡፡ የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡

በሌላ በኩል በሀገራችን ያለው የሰላም ሁኔታ በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ይህም ሂዶ ሂዶ ቤተ ክርስቲያንንና ሕዝብን፣ ሀገርን ልማትን መጕዳቱ የማይቀር ነው፡፡

በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መሥራት ይኖርብናል፡፡

ከዚህም ጋር የዛሬው ጉባኤ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓቢይ ተልእኮ ለመፈጸም እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተጀመሩትን ወሳኝ ስራዎች በዝርዝር በማየት ውሳኔ የምናሳልፍበት ጉባኤ ይሆናል፡፡

ከዚህም ሌላ በተፈጠረው አላስፈላጊ ከባድ ጦርነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተፈናቀሉ ምእመናን ልጆቻችንን በፍጥነት ደርሰን የምናጽናናበትንና የምንደግፍበትን ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ማየት ይኖርብናል፡፡

በመጨረሻም

በአሁኑ ጊዜ ኣላስፈላጊ በሆነ የእርስ በርስ ግጭት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ግጭቱን ኣቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ ኣባታዊ ጥሪያችንን በአጽንዖት እያስተላለፍን የ፳፻፲፭ ዓ.ም የረክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት የተከፈተ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እናበስራለን።

 

እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክልን!

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

አዲስአበባ – ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on LinkedIn
  • Share on Telegram
  • Share by Mail
https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/abune-matias-1.png 430 430 gssu https://eotc-gssu.org/a/wp-content/uploads/logo-2-1-300x74-1.png gssu2023-05-13 17:21:542023-05-13 17:45:51የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር
Search Search

Recent Posts

  • የሦስተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የኹለተኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የአንደኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ይዘት
  • የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
  • ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።

Archives

  • April 2026
  • September 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • May 2025
  • April 2025
  • October 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • July 2022
  • June 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
© Ethiopian Orthodox Church Global Sunday School Union | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
  • Link to Youtube
  • Link to Telegram
  • Link to TikTok
Link to: ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤ የካህናት፣የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጭምር እንጂ! Link to: ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤ የካህናት፣የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጭምር እንጂ! ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤... Link to: ቤተ ክርስትያን እና አመራሮቿ Link to: ቤተ ክርስትያን እና አመራሮቿ ቤተ ክርስትያን እና አመራሮቿ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top