ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሐት
ምሕረቱ ለዘላለም ነውና/2/
ጾምን እንጹም ሰውንም እናፍቅር
አዝ . . .
ሰንበትን እናክብር ጽድቅንም እንፈጽም
አዝ . . .
ከእህል ብቻ አይደለም ጾምን መጾም
ክፉ ከመናገር መከልከል ይቅደም
አዝ . . .
ፈተናውስ ለርሱ ለጌታችን አልቀረም
አዝ . . .
ምሳሌውን ከርሱ ከጌታችን እንውሰድ
አዝ . . .

ገዳመ ቆሮንቶስ የትምህርት ገበታ
ባንቺ ተፈተነ መምህርና ጌታ
አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ጹመህ
ሦስትን ጥያቄዎች ፈታኝ ቢያቀርብብህ
በፍጹም ትሕትና ታግሠህ ታግሠህ
ለኛ አርአያ ልትሆን ፈተና ተቀበልህ
አዝ . . .
ጌታ ሆይ ፈታኝህ አንተ ያሳፈርኸው
ይከታተላል ዛሬም ጠላታችን ነው
በረቂቅ ጥበብህ በማንመረምረው
ድል አድራጊው ጌታ እባክህ ድል ንሣው
ይኽ ክፉ መንፈስ የማይታይ ጎልቶ
ትዕቢትና ስስት መርዝ ሆኖ ገብቶ
ሊፈጀን ነውና እርስ በርስ አጣልቶ
ጌታ ሆይ አሳየን ዝክረ ስሙ ጠፍቶ
አዝ . . .
ሰው በእንጀራ ብቻ ሊኖር እንደማይችል
ለመጣብህ ፈታኝ በግልጽ አውጀሃል
ኃይል ስለሌለን በምንበላው እህል
አቤቱ አይለየን ዘወትር ያንተ ቃል
አዝ . . .
(መዝሙረ ሐዋዝ)

         (አማን በአማን በሚለው ዜማ)
የነፍሳችን ቤዛ የቅዱሳን ሀብት (2)
ጸጋን የሚያሰጠን ጾም ነው መድኃኒት (2)
የእስራኤል ልጆች በሙሴ ሲመሩ (2)
በፍጹም ጸሎት ባሕሩን ተሻገሩ (2)
ቅዱሳን አባቶች ጾም ነው ጋሻቸው(2)
ወደ ሕይወት መንገድ የሚመራቸው (2)
ክፍላችን እንዲሆን ከቅዱሳን ጋራ (2)
ፍቅር ቤታችንን በጸሎት እንስራ(2)
ልባችንም ይሁን የጸሎት ጎዳና(2)
የእግዚአብሔር መንግሥት እድንወርስ በጤና (2)

        (በጌቴ ሴማኔ በሚለው ዜማ)
ፍቅርና ሰላምን ታፈራለች ጾም
ፍጻሜ የሌለው እስከ ዘለአለም
የጾምንም ፍሬ ሁላችን ዐውቀን
ለጸሎት እንትጋ ፍሬዋ አይለፈን
አምላክ ተፈተነ በክፉ ጠላት
ጾምን ሲመሠርት ስለኛ ሕይወት
አምላክ ተሸከመ ሕመማችንን
የሕይወትን ውሃ ከጎኑ ሰጠን
ሕዝቦችህን ጠብቅ ከክፉ ፈተና
ቅዱስ አምላካችን ኃይላችን ነህና
(መዝሙረ ስብሐት)

            (የአብርሃም አምላክ በሚለው ዜማ)
ነቢዩ ዳንኤል በጾም ስላመነ
ከአንበሶች ጒድጓድ ሕይወቱን አዳነ
ኤልያስ የወጣ በእሳት ሠረገላ
በጾም በጸሎት ነው አይደለም በሌላ
የነፍስን ቍስል ጾም ታድናለች
የሥጋን ፍላጎት እያደከመች
እስቲ ልብ እናድርግ እናስተውል ደግሞ
ጌታ ለሐዋርያት ያላቸውን ቀድሞ
ይህ ርኩስ መንፈስ ሊወጣ የሚችል
በጾም በጸሎት ነው እንደ ወንጌሉ ቃል
(መዝሙረ ስብሐት)

መመኪያዬ አንተ ነህ የነፍሴ መዳኛ/2/
ተመልከት ወይኔ አትስጠኝ ለዳኛ
ሕይወቴን ላንተ/2/ ብያለሁ
አምላክ የኔ ጌታ የት አገኝሃለሁ
ከበደሌም አንጻኝ ደግሞም ከኃጢአቴ/2/
በመንፈስ ይቀደስ መላው ሰውነቴ
አዝ . . .
ዐቀበቱ ልቤ በጭንጫው ትዕቢት/2/
አሸብርቆ ነበር አይፈርስ መስሎት
አዝ . . .
የጾም ንጉሥ መምጣት ስለተነገረ/2/
መደልደል አለበት እየተሰበረ
አዝ . . .
ሶስናን ያዳንካት ከሐሰት ምስክር/2/
እኔንም አድነኝ ካልታሰበ ነገር
(መዝሙረ ስብሐት)

          (ሰብሕዎ በጸናጽል በሚለው ዜማ)
ለጾም እናድላ በአንድነት ሆነን
ዋጋችን በሰማይ እንዲከፈለን
በንጹሕ እንምራ ሕይወታችንን
የገነት በር እንዳይጠፋብን
በንስሓ እናንጻት ነፍሳችንን
ትዕዛዙን እንጠብቅ የአምላካችንን

ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት (2)
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ አሥሮነ ቃላት (2)
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም እና በጸሎት (2)
ተቀበለ ሙሴ ኦሪትን(ጽላትን) አሥርቱ ቃላትን(2)
(ቅዱስ ያሬድ)

ክርስቶስኒ ጾመ
በእንቲአነ መድኃኒነ ጾመ
አርአያ ዚአሁ ከመ የሀበነ/2/
(ቅዱስ ያሬድ)

ይጹም ዓይን ይጹም ልሳን

እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ሕሱም

በተፋቅሮ ወበሰላም

         ዐይን ይጹምአንደበትም ይጹም

        ጆሮም ይጹም ክፉ ከመስማት

        በፍቅር እና በሰላም

                    (ቅዱስ ያሬድ)

ዘጾመ ወጸለየ ወሰአለ (2)
እሙነ ይነስእ ዕሴቶ (2)
የጾመ የጸለየ የለመነ (2)
እውነት ነው ዋጋውን ይቀበላል (2)
(ቅዱስ ያሬድ)