የ2014 ዓ.ም መስቀል በዓል የሰ/ት/ቤቶች ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገለጸ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በደማቁ ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት ትርኢትና ወረብ ለማቅረብ ከአዲስ አበባ ከሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ቁጥራቸው ከ5500 ባላይ የሆነ ወጣቶች ለተከታታይ 25 ቀናት ዝግጅት አደረጉ።

በበዓሉም የሰሜን ክፍለ ከተማ ሰንበት ተማሪዎች ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለዓለማችን በሚል ርዕስ መንፈስዊ ትርኢት ፣ የምሥራቁ ክፍለ ከተማ ደግሞ የመስቀል ጉዞን የሚያሳይ መንፈሳዊ ተውኔት እንዲሁም የምዕራብ ክፍለ ከተማ ቤተ ክርስቲያን ከሁሉም በላይ ናት የሚል ትርኢት ሲያቀርቡ የደቡብ እና የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በቅንጅት ወረብ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።