መሠረታዊ መረጃዎች

አጭር መግለጫ

ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በዓለም አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የሚመሠረት በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት ያለውን አገልግሎት ወጥ ለማድረግ የሚሠራ መዋቅር ነው፡፡

ራእይ

በ2030 የሰንበት ት/ቤቶች ተቋማዊ አቅም ጎልብቶና ተደራሽታቸው ሰፍቶ ፣ አባላት በወጥ ሥርዓተ ትምህርት ሁለንተናዊ አቅማቸው ተገንብቶ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራዊ ጉዳዮች ጉልህና የተናበበ ሚና የሚጫወቱ ሆነው ማየት

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት አባላትን በተደራጀ መዋቅራዊ አንድነት፣ ወጥ በሆነ የትምህርት ሥርዓትና ግብዓት በማስተማር፣ የአገልጋዮችን አቅም በማሳደግ፣ ዘመኑን በዋጀ አሠራር፣ በተቀደሰ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን እና ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያገለግሉና የሚጠብቁ አገልጋዮችን ማፍራትና ማሰማራት

እሤቶች

  • እግዚአብሔርን መፍራት
  • ሰውን ማክበር
  • በፍቅር የሆነ አገልግሎት
  • ክርስቲያናዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነት
  • ሁሉን በጥበብና ለመንፈሳዊ ዋጋ ማድረግ
  • ዓለም ዐቀፋዊ አገልግሎትን ማስፋት
  • ፅናትና ምስክርነት
  • ዘመኑን መቅደም፣ መዋጀት