የሦስት ወር የክረምት ፕሮጀክት ሥራ ማስታወቂያ – የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
፩. ለሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት የትግሪኛ ትርጉም ባለሙያ
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️ በሰንበት ት/ቤት እና ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስጻሚነት ወይም ክፍል ተጠሪነት ያገለገለ/ለች
▶️ በሰንበት ት/ቤት በማስተማር መምህርነት ልምድ ያለው
▶️ቢያንስ በሰንበት ት/ቤት የሚሰጡ ትምህርቶችን ያጠናቀቀ/ች
▶️በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/ች
▶️የኮምፒወተር አጠቃቀም መሠረታዊ ዕውቀት ያለው/ያላት
፪. ለሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት የእንግሊዝኛ ትርጉም ባለሙያ
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️ በሰንበት ት/ቤት እና ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስጻሚነት ወይም ክፍል ተጠሪነት ያገለገለ/ለች
▶️ በሰንበት ት/ቤት በማስተማር መምህርነት ልምድ ያለው
▶️ቢያንስ በሰንበት ት/ቤት የሚሰጡ ትምህርቶችን ያጠናቀቀ/ች
▶️በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/ች
▶️የኮምፒወተር አጠቃቀም መሠረታዊ ዕውቀት ያለው/ያላት
፫. የሥልጠና አስተባባሪ
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️ በሰንበት ት/ቤት እና ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስጻሚነት ወይም ክፍል ተጠሪነት ያገለገለ/ለች
▶️ በሰንበት ት/ቤት በማስተማር መምህርነት ልምድ ያለው
▶️ በሰንበት ት/ቤት አሰልጣኝነት ልምድ ያለው/ያላት
▶️በመምህርነትና በአሰልጣኝነት ስልጠና የወሰደ
▶️በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/ች
▶️የኮምፒወተር አጠቃቀም መሠረታዊ ዕውቀት ያለው/ያላት
፬. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️በሰንበት ት/ቤት እና በግቢ ጉባኤያት ያገለገለ/ለች
▶️በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች
፭. የግራፊክስ ዲዛይን ባለሙያ
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️በሰንበት ት/ቤት እና ግቢ ጉባኤያት ያገለገለ/ለች
▶️በሰንበት ት/ቤት ሥነ ጽሑፍና ሥነ ጥበባት፣ መዝሙር፣ ሚዲያ ክፍሎች ያገለገለ/ለች
▶️በዘርፉ ስልጠና የወሰደ እና ፍላጎት ያለው/ያላት
▶️በዘርፉ ሙያ ወይም ተመሳሳይ የተመረቀ/ች
፮. የሥዕል ባለሙያ
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️በሰንበት ት/ቤት እና ግቢ ጉባኤያት ያገለገለ/ለች
▶️በሰንበት ት/ቤት ሥነ ጽሑፍና ሥነ ጥበባት፣ መዝሙር፣ ሚዲያ ክፍሎች ያገለገለ/ለች
▶️በዘርፉ ስልጠና የወሰደ እና ፍላጎት ያለው/ያላት
▶️በዘርፉ ሙያ ወይም ተመሳሳይ የተመረቀ/ች
▶️ከምፒዩተር ዕውቀት ያለው/ያላት
፯. ዳታ ኢንኮደር
ተፈላጊ ልምድ/ችሎታ
▶️በሰንበት ት/ቤት እና ግቢ ጉባኤያት ያገለገለ/ለች
▶️በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተመረቀ/ች
ለኹሉም የሥራ መስኮች፡-
✳️ ጾታ አይለይም፣
✳️የስራ ቦታ:- አዲስ አበባ፣
✳️የፕሮጀክቱ የቆይታ ጊዜ ከሐምሌ 1/2017 እስከ መስከረም 30/2018
አመልካቾች ሊያሟሉዋቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡-
✳️ የሰ/ት/ቤት አባል የሆነ/የሆነች ብቻ፣
✳️ በአባልነት ከተመዘገቡበት አጥቢያ ሰንበት ት/ቤት የአባልነት ማረጋገጫ ማቅረብ ፣
ለመመዝገብ ከዚህ በታች የተቀመጠውን የመመዝገቢያ ቅጽ እስከ ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ድረስ ሞልተው ይላኩ፡፡