የሥነ ጥበብ ትምህርት መጻሕፍት
በሥርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ማሻሻያ መሠረት ከስምንተኛ (8ኛ) ክፍል ጀምሮ እስከ አስራ ኹለተኛ (12ኛ) ክፍል ድረስ የሥነ ጥበብ/ሕይወት ክህሎት እንደ 7ኛ ክፍለ ትምህርት ሆኖ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
✍️ በመሆኑም ከ8ኛ እስከ 10ኛ ባሉት ክፍሎች ከመጽሐፉ ኅትመት ጋር አብሮ በምዕራፍ አንድ ብቻ ተካቶ የታተመ ሲሆን ቀሪዎቹን የመጻሕፍቱን ምዕራፎች ለመምህራን ማስተማርያ ይሆን ዘንድ በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መካነ ድር ላይ በመለቀቁ በማውረድ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
✍️ መልዕክት ለሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች
👉 የትምህርት አሰጣጡን በተመለከተ ታትመው በተሰራጩት መጻሕፍት መግቢያ ላይ የተጠቀሰ በመሆኑ አንብባችሁ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን።
የመጻሕፍቱን በእነዚህ ሊንኮች ማግኘት ይችላሉ፦
- ሥነ ጥበብ (ሥነ ጽሑፍ ስነ ሥዕል) ትምህርት 8ኛ ክፍል
- ሥነ ጥበብ (የሕይወት ክህሎት አንድ) ትምህርት 9ኛ ክፍል
- ሥነ ጥበብ (ብራና ሥራ፣ ድጉሰት፣ ኪነ ሕንጻ) 10ኛ ክፍል
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
